Friday, June 29, 2012

የብሄር ትርጉሙ

የብሄር ትርጉሙ ባልፉት ሃያ ኣመታት ውሰጥ በውነት ከቸኩ ቃሎቸ መካከል አንዱብሄርየሚባለው ቃል ነው። በመሰረቱ ብሄር የሚለው ቃል መነሻው ኣማርኛ ነው። ይታወቅበት የነበረውም ትርጉም የትውልድ ኣካባቢ ነው። ለዚህም ነው ተስፋ ስላሴ ብሄረ ቡልጋ፣ አፈወርቅ ገብረየሱስ ብሄረ ዘጌ፣ ምናምን የሚባለው መሰለኝ። በዚሁ ሂሳብ ከሄድን ባሁኑ ሰኣት ማለት የምንችለው ኣቶ ሃጎስ በላይ ኣዲስ ኣበባ ከተወለዱ ብሄረ ኣዲስ ኣበባ ክቡር ዶክቶር ብርሃኑ ነጋ ብሄረ ደብረዘይት፣ እምሻው ለጥ ይበሉ ዘብሄረ ሃረር፣ ቶላ ድሪባ ብሄረ መንዝ፣ ክቡር ኣቶ ኣንዳርጋቸው ጽጌ ብሄረ ኣዲስ ኣበባ፣ እያለ ይቀጥላል ማለት ነው። ታዲያ ወያኔዎች ለምን ይህን ቦታ ወይም የግዛት ስም ወስደው ጎሳ ፖለቲካ ላይ እንደለጠፉት ኣይታወቅም። ምን ኣልባት የጎሳ ፖለቲካ ኣሳፋሪ በመሆኑ ጎሰኛ የሚለውን ስም ለመሸፈን ይሆናል። የጎሳ ፖለቲካ ቅድስና ያለው ስላልሆነ በፊት ለፊት ለመጥራት ያፍሩበታል። ዋናው ደሞ የቃላቱ ጨዋታ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ መንግስት የሚያራምደው ፖለቲካ ታእታይ ቅርጹ (deep structure) ባህላዊ ቡድኖችን ሚና እንዲለዩ በማድረግ ግጭት ማራገብ በዚያም ሾልኮ በስልጣን መሰነባበት ነው። በመሆኑም የወያኔዎች ፖለቲካ ብሄር ምናምን ሳይሆን ባህላዊ ቡድነኝነት ፖለቲካ ኣራማጆች ናቸው ይህ ኣይነቱ ፖለቲካ የሳተው ትልቅ መሰረታዊ ነገር ቡድኖችን ገስጋሽ እና ለውጥ ናፋቂ ተፈጥሮ ነው። በተለይ በዚህ ክፍለ ዘመን ሳይንስ ራሱ የኣለምን ቁሳዊ ባህል እያዋሃደው በመጣበት ጊዜ እንዲህ ኣይነቱ በባህል ቡድን ላይ የሚሰራ ፖለቲካ ማደሪያ የለውም። በሃጋራችን ይህ ፖለቲካ ከባህል እና ቋንቋ ልዩነት ጋር ተጣብቆ ሲመጣ መጀመሪያ የተጋጨው ከየ ባህላዊ ቡድኑ እየቀደሙ በኣለም ኣቀፉ የባህል ልውውጥ እና በርስበርሱ የባህል ውህደት ጎዳና ላይ ካሉ ገስጋሽ ዜጎች ጋር ነው። ርግጥ ነው የባህልና የቋንቋ ልዩነት በኢትዮጵያ ውስጥ ኣለ። ታዲያ የኣስተዳደር ጥበብ ሲታሰብ 90 የፖለቲካ ድርጅት ኣቋቁሞ እኔ እቀድም እኔ መጀመሪያ በሚል ጨዋታ ኣይደለም የምንተዳደረው። የቡድን ፖለቲካ ውስጠኛ ስሜት እኮ ቋንቋን የወሰን መከለያ ድንጋይ ኣድርጎ በኣንድ ልል በሆነ ማእከላዊ መንግስት ስር መኖር ነው። ይህ ደሞ ኣንድ ቀን ፖለቲካው ሲፈርስ ብትንትናችን እንዲወጣ ያደርጋል። የኔን ባህል ኣትንካ እኔም ያንተን ኣልነካም ኣይባልም። የኔን ቋንቋ ኣትንካ እኔም ያንተን ኣልነካም ኣይባልም። እንዲህ ኣይነቱ ነገር ብንፈልገውም እንኩዋን ኣለማቀፋዊው ነባራዊ ሁኔታ ኣይፈቅድልንም። ይሄም ባህል መጠበቅ ማለት ኣይደለም። ኣንዳንዴ ደሞ ለውዽዽር ወይም ለክርክር መቅረብ የሌለባቸውን ማተላያ (false goods) እያመጡ ህዝብን ያደናግራሉ። የቡድን መብት ይቅደም ወይስ የግለሰብ መብት ይቅደም፧ በመሰረቱ የመቀዳደም ጉዳይ ኣይደለም ዋናው ነገር ዴሞክራሲ ራሱ ይቅደም። እሱ ሲቀድም ቤቱን በሰው ልጆች የመጨረሻ የልዩነት ቅንጣት ላይ ይሰራና ቡድኖችን ይንከባከባል። ይህ ማለት መጀመሪያ ግለሰብ ከዘያ ቀስ ብሎ ቡድን ማለት ኣይደለም። እንዲህ ኣይነቱ በተግባር ኣይገጥምም ከገጠመም ጤነኛ ዴሞክራሲ ኣይሆንም። የሰው ልጅ ለብቻውም ከሰው ጋርም ነው የሚኖረውና። የቡድንም የግልም ህይወቱ እሽቅድምድም ውስጥ ሳይገቡ ሊንከባከባቸው ይፈልጋል። ዶሮዋ ናት የምትቀድመው ወይስ እንቁላሉ የሚል የጊዜ ማጥፊያ ክርክር እዚህ ጋር ኣይሰራም። መሽቀዳደማቸው ሳይሆን ኣንዱ ያላንዱ ያለመኖራቸውን ማሳቡ የበለጠ ይጠቅመናል። እግዚኣብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ
geletawzeleke@gmail.com

No comments:

Post a Comment

Geletaw Zeleke's New Book *** ETHIOPIAN POLITICS የኢትዮጵያ ፖለቲካ

ይህ መጽሀፍ የማንነት ፖለቲካ እንዴትና ከየት እንደተነሳና ያለውን ችግሮች በዝርዝር ያስረዳል:: ዛሬ የኢትዮጵያ ሕዝብ ማህበረሰባዊ ግንኙነቶች ፈራርሰዋል። ደራሲው የሃገራችን መሰረታዊ ችግር የማህበረ ፖለቲካ ነው ይላል። ...