በገለታው ዘለቀ
በጣም ከሚገርሙኝ እሰጥ ኣገባ ክርክሮች መካከል ኣንዱ ይሄ ኢኮኖሚ መጀመሪያ ከዚያ ዴሞክራሲ ወይም የለም ዴሞክራሲ መጀመሪያ ከዚያ በሁዋላ ልማት የሚባለው ነገር ነው። ለዚህ ክርክር መድረክ የሚያዘጋጅ ሰው ምሱ መጀመሪያ ነገር መቼ ዴሞክራሲና ልማት ተጣልተው ኣየህ? መቼ እኔ እቀድም እኔ እቀድም በሚል ተጠላልፈው ሲውድቁ ኣየህ? ብሎ ቀንዱን ነበር ።
ዕንደ ዕውነቱ ልማትና ዴሞክራሲ ወዳጆች ናቸው። ደመኞች ኣይደሉም። ኣንዱ ኣንዱን የሚያዘገይ ኣይደሉም።ዴሞክራሲ ሲጀመር የታል ልማት ብሎ ይጠይቃል፤ ልማት ሲጀመር ደሞ እኔ ላንተ የሚሆን በጀት የለኝም ኣይለውም ዴሞክራሲን። ኣንዳቸው ኣንዳቸውን ለመጉዳት ለመጣጣል የማይፈላለጉ ናቸው። እንዴውም ልማት በሰፊው ትርጉሙ ዴሞክራሲን የሚጠቀልል ሲሆን ዴሞክራሲ በሰፊው ትርጉሙ ልማትን ዕቅፍ ኣርጎ ይይዛል ።
ይሁን አንጂ ታዲያ ኣንዱን ችላ ብሎ ኣንዱን ኣጥብቆ ይዞ መሄድ ኣይቻልም ማለት ኣይደለም። መንግስታት ዳቦ ብላ የመብትን ነገር ኣታንሳ ሊሉ ይችላሉ። ዕነዚህ መንግስታት ራሳቸውን “ልማታዊ መንግስት” ብለው ልማትን የኢኮኖሚ ዕድገት ብቻ ኣድርገው ኣጥበው በመተርጎም የስልጣን ጥም ሊቆርጡበት ይሞክራሉ ። ራሱ ህዝቡ ለፍቶ ያመረተውን ምርት እየቆጠሩ ይህ የተሰራው በኛ ነው ዕያሉ በህዝብ ጉልበት ህዝብን ጉቦ ሊያበሉ የሚዳዳቸው ጮሌዎች ናቸው።
የለም ያለ ዴሞክራሲ ልማት ኣይቻልም ሲሏቸው የጅል ፈጣን መልሳቸው ቻይናን ኣታይም? ነው። ቻይና በመሰረቱ የደላት ኣገር ኣይደለችም ዕኮ ። ህዝቦቹዋ የሃይማኖት ነጻነታቸው ኣደጋ ላይ ያላበት፣ የሲቪል መብታቸው የተሸረሸረባቸው፣ ሰባዊ መብታቸው የጎደለባቸው፣ ባጠቃላይ የዴሞክራሲ ርሃብ ና ጥማት ያለባት ሃገር ናት። እንዴት ሆና ነው ቻይና በምሳሌነት የምትጠራው፧ ቻይና የኢኮኖሚ ዕድገት ዴሞክራሲ ሊያመጣ ዕንደሚችል መች ኣስመሰከረች?
የኢኮንሚ ዕድገት ለሰው ልጆች ሁለንተናዊ ልማት ኣስተዋጽኦ ካላደረገ ምን ጥቅም ኣለው? ይልቁን ቻይና ዴሞክራሲን የናፈቀች ትመስላለች ወደፊትም በርግጥ ህዝቡዋ ታግሎ መብቱን ማስከበሩ ኣይቀሬ ነው በርግጥ።
የሰው ልጅ ዕኮ ሆድ ብቻ ኣይደለም ፍላጎትና ምርጫ ኣለው። ዳቦ ብላ ግን የመብትን ነገር ኣታንሳ ሊባል ኣይገባውም ።የሰው ልጅ ልማትም ዴሞክራሲም ያስፈልገዋል። ልማትና ዴሞክራሲ ደሞ ኣብረው ቢሄዱ ይፈጥናሉ እንጂ ኣይደክሙም።ይሄ በመርህ ደረጃ ያለው ዕምነት ነው።
ወደኛው ቤት ጉድ ስንመጣ ግን ዕድገቱስ የት ነው ለመሆኑ ቢያንስ ዳቦህን ብላ የመብት ነገር ኣታንሳ ለማለት ዳቦውስ የታል ነው ጥያቄው።
ሌላው የሚገርመኝ ነገር ደሞ በኢትዮጵያ ውስጥ የኢኮኖሚ ዕድገት ኣለ የለም ብለው ሰዎች ለክርክር ሲነሱ ነው። ክርክር በመሰረቱ በሁለት በሚመስሉ ነገሮች መካከል የሚደረግ የመተማመን ፍልሚያ ነው። ኢትዮጵያ ኣድጋለች ኣላደገችም በሚል የሞቀ ክርክር ማድረግ የሚቻል ኣይመስለኝም። ሃቆች በየሜዳው ኣፍጠው በነሱ ላይ ኣሉ የሉም ማለት ኣይቻልም። የብዙሃኑ ኑሮ በኛ ክርክር ኣይለወጥምና። ላለፉት ፰ ኣመታት በጥንድ ቁጥር (double digit) ኣደግን ኣለም በኛ ዕድገት ተደነቀ ይልና ሳይጨርሰው ደሞ ሚሊዮኖች ተርበዋልና ዕርዳታ ከውጭ ያስፈልገናል ይላል። ኣሁን በዚህ ላይ ምን ክርክርና ግራ መጋባት ያስፈልጋል? ለነገሩ የመንግስት ደብል ዲጂት ፕሮፓጋንዳ ህዝብ ያምነዋል ከሚል ኣይመስለኝም ይልቁን በኢኮኖሚ ማደጋችን ቀርቶ ወደ ሗላ ስለ ሄድን ቢያንስ ኣድገናል ስንል የምንፈጥረው ውዢምብር ተቃዋሚዎቻችንን ወደ ኣንድ መካከለኛ ቦታ (position) ሊያመጣልን ይችላል በዚህም የሗሊት ጉዙዋችን ይደበቅልናል ብለው ኣምነው ይሆናል። ልማታዊ ብሎ ራሱን ከሰየመ ደሞ ጸረ ዴሞክራሲ ከሆነ መንግስት የሰው ልጅ ሁለንተናዊ ልማት (human development) ኣይጠበቅም።
ገለታው ዘለቀ
geletawzeleke@gmail.com
geletawzeleke@gmail.com
No comments:
Post a Comment