
—አክሎግ ቢራራ (ዶር) ኢኮኖሚስት፤ በዓለም ባንክ ከፍተኛ አማካሪ፤ ደራሲና የሰብአዊ መብቶች አክቲቪስት
ሀገራችን ኢትዮጵያ የረጅም ዘመናት አኩሪ ታሪክና ባህል ባለቤት ሆና ሳለ፣ እኛ ኢትዮጵያዊያን ከድህነት፣ ከኢፍትሃዊ ስርዓትና ውስጣዊ ግጭቶች እንዴት መላቀቅ ተሳነን? ሀገራችንን ከዚህ አስጨናቂ ስጋት አውጥተን ዴሞክራሲ፣ ፍትህ፣ እኩልነት፣ ነጻነት፣ ሰላምና ብልጽግና የሰፈነባት ሀገር ለማድረግስ ምን ማድረግ አለብን? በተለይም አሁን ከገባንበት አሳሳቢ ማህበረ-ፖለቲካዊ ቀውስ ለመውጣት፣ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የሚከበርበት ስርዓት ለመገንባት ያሉን አማራጮችስ ምን ምን ናቸው? የአቶ ገለታው መጽሃፍ እነዚህንና እነዚህን የመሳሰሉ ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚያስችሉ፣ በጥናትና ምርምር፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ የረጅም ዘመናት ታሪክ፣ ብዝሀነትና ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረቱ ጠቃሚ ሃሳቦችን ይዟል። መጽሃፉ በስፋት ካነሳቸው በርካታ ነጥቦች መካከል፣ “በስምምነት ላይ የተመሰረተ ባህላዊ አንድነት (ስባአ)” የሚል አዲስ ጽንሰ-ሃሳብ ይገኝበታል። ይኸውም ኢትዮጵያን ከተተበተበችበት ኢፍትሃዊ አገዛዝና ማህበረ-ፖለቲካዊ ቀውስ አውጥቶ፣ የተሻለ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት፣ ሰላማዊ አብሮነትንና ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር፣ የኢትዮጵያ ህዝብ በረጅም ዘመናት የህይወት ተሞክሮው ያዳበራቸውን አኩሪ ባህሎቹንና የጋራ እሴቶቹን መሰረት ማድረግ ይገባል የሚል ነው። ይህ በመጽሃፉ ውስጥ በፖለቲካዊ ሳይንስና ባህል ጥናት ትውሮች ተደግፎ በጥልቀት የተተነተነው ሃሳብ፣ የሀገራችንን ፈርጀ-ብዙ ችግሮች ለመፍታት አንድ ውጤታማና ወቅታዊ አማራጭ ሊሆን እንደሚችል አምናለሁ።
—አብርሃም ዓለሙ፣ የኢትዮጵያ ሰነ-ጽሁፍና ባህሎች መምህር
—አብርሃም ዓለሙ፣ የኢትዮጵያ ሰነ-ጽሁፍና ባህሎች መምህር
ገለታው ዘለቀ በስምምነት ላይ የተመሰረተ ባህላዊ አንድነት ንድፈ ሃሳብ መሃንዲስ ሲሆን በኢትዮጵያ ፓለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ገንቢ አስተያየቶች የሚያቀርብ ነው።
http://africaworldpressbooks.com/ethiopian-politics-by-geletaw-zeleke/
http://africaworldpressbooks.com/ethiopian-politics-by-geletaw-zeleke/
No comments:
Post a Comment