Friday, June 29, 2012

ዛሬ ኦነግ ነገ ደሞ ኦብነግ እልል በይ አገሬ

By: Geletaw Zeleke

ፖለቲካ በሁለት መሰረቶች ላይ የቆመ ሲሆን አንዱ ዶግማ ሌላኛው ደሞ ቀኖና ነው። ዶግማው ምን ጊዜም ኣይለወጥም። ዘመን ኣልፎ ዘምን ሲተካ ትውልድ ኣልፎ ትልድ ሲተካ ለሁል ጊዜም ይኖራል። የፖለቲካ ድርጅቶችም የሚሞቱለት ጉዳይ ቢኖር ይሄ ነው። ፍትሕ ዴሞክራሲ ነጻነት ለምሳሌ ዶግማዎች ናቸው።
ኣንድ ድርጅት ሲቆም ቀኖናዎችም ኣሉት። እነዚህ ቀኖናዎች የድርጅቶቻችን የትግል ስልቶች ወይም ሌሎች ግባቶች ሊሆኑ ይችላሉ። ቀኖና ናቸው እና አንደ ሁኔታው ዘመን ሊለውጣቸው ይችላል። ይሁን እንጂ ኣንዳንድ የፖለቲካ
ድርጅቶች ቀኖናውንም ዶግማውንም ኣደባልቀው ዘመን ሲለወጥ ኣንለወጥም ብለው ችክ በማለታቸው ከቆሙለት ህዝብ ይፋታሉ። ደሞም ካሰቡት ለመድረስ ሳይችሉ ይቀራሉ።
ፖለቲካ የሰው ልጅን ገስጋሽ የሆነ ኣመለካከት ስራዬ ብሎ ተክትሎ የሚሄድ ጥበብ ነው።በቅርቡ ከኦነግ የወጣው መግለጫ የሚያሳየው የኦነግ መሪዎች ምን ያህል ከግል ፍላጎት እና ከግትርነት በላይ የኢትዮጵያዊያንን መከራ ለማሳጠር የቆረጡ ኣገር ወዳድ ጀግኖች መሆናቸውን ነው።
ለነነገሩ ድሮም ቢሆን የመገንጠል ጥያቄ የኦነግ ዶግማው ሳይሆን ቀኖናው ነበር። ይህ ቀኖና ደሞ ለተባለው ዋና ኣላማ ማለትም ለነጻነት ለፍትሕ ለዴሞክራሲ መስፈን አንደ መንገድ (means) ይሆናል ከሚል ስሜት የመጣ ነበር ይህ የትግል ስልት ግን ለኦሮሞ ህዝብ የሁዋላ ዴሞክራሲ ፍትሕ በፍጹም ዋስትና እንደሌለው ኦነግ
ኣጥብቆ የተረዳ ለመሆኑ የበቀደሙ መግለጫ ያሳያል። የኦነግ መሪዎች በወሰዱት ርምጃ ሁሉን ኢትዮጵያዊ የሚያኮራ እነዚህን መሪዎችም በለቀ የሞራል እሴት ላይ የሚሰይማቸው ተግባር ነው።
የዚህ የኦነግ ሃላፊነት እና ብስለት የተመላበተ ውሳኔ በሃገራችን የነጻነት ትግል ላይ የሚከተሉት ኣዎንታዊ ተጽዕኖዎች ያሳርፋል የሚል እምነት ያሳድርብናል
) ሌሎች ዘውግ ተኮር የሆኑ ድርጅቶችን ያነቃል በሃገራችን ወስጥ በነጻነት እጦት ሆድ ብሶት ለሚታገለው ኦብነግ የዚህ የኦነግ ያቁዋም ለውጥ ይነሽጠዋል የሚሉ
ኢትዮጵያዊያን ኣያሌ ይሆናሉ። ኣብነግ ልክ አንደ ኦነግ ኣካሄዱን ኣይቶ ቀኖናውን ሽሮ ለመላው ኢትዮጵያውያን ነጻነት እኔም አንደ ኦነግ የሚልበትን የሞራል ስንቅ ከኦነግ ኣግኝቱዋል።በኣጠቃላይ የኦነግ የኣስተሳሰብ ተሃድሶ ትልቅ ትምህርትን ለመላው ኢትዮጵያዊ ኣስተላልፏል።
)በተራ ዜጎች መካከል መተማመንን ፍቅርን ያዳብራል ፖለቲካ ከዘውግ ጋር ተጣብቆ ሲመጣ በተራ ዜጎች መካከል የስነ ልቡና ክፍተት መፍጠሩ ኣይካድም። በተለይም የፖለቲካ ድርጅቶች ጫፍ ሄደው እስከ መገንጠል ሲመኙ በዜጎች መካከል ያንድነት ስሜት እየኮሰሰ በዚያው ልክ የመለየት ስሜት እያደገ መምጣቱ ኣይቀሬ ነው። የኦሮሞ ህዝብ ከተቀበለው ግፍና በደል የተነሳ ለኔ መብት የቆመ ስቃዬ የተሰማው ብሎ ያመነው ባንጻራዊነት ኦነግን ነው ብሎ መናገር ይቻላል። ይሁን እንጂ ኦነግ የኦሮሞን ህዝብ ነጻነት ለማምጣት የሚሄድበት የነበረው የመገንጠል ጥያቄ ጉዳይ ግን የኦሮሞ ህዝብ መንገድ ነበር ማለት ኣይቻልም። የኦሮሞ ህዝብ
የነፍሱ ጥያቄ የነጻነት እንጂ የኦነግ የመገንጠል ኣጀንዳ በኦሮሞው ዘንድ የከበረ ጥያቄ ኣልነበረም በመሆኑም ኦነግ ከመቸውም የበለጠ ዛሬ በኦሮሞዎች ዘንድ ተቀባይነት ያገኛል። በፊት የነበረውን የህዝቡን ስጋት ሁሉ ኣውጥቶ የሚጥል፤ ሃላፊነት የተሞላበት ቸርነት ያለበት ዉሳኔ በመሆኑ የኦሮሞ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዊ ወገኖቹ ጋር በመተማመን ቁጭ ብሎ የሚጫወተው የሚጋራው ብስራት ነው ) ብሄራዊ ስሜታችንን ለመጠበቅ ለምናደርገው ትግል ኣዎንታዊ ኣስተዋጾ ኣለው በዚህ ዘመን ኣገራችንን የገጠማት ፈተና የነጻነት ጉዳይ ብቻ ኣይደለም። ገዢው መንግስት ብሄራዊ ስሜትን እያንኳሰሰ ልዩነትን እያሰፋ በመሄድ ነው በስልጣን መቆየት የሚቻል የሚመስለው። በዚህ ላይ ላለፉት ሃያ ኣመታት
ሲሰራ ነው የቆየው። ታዲያ ይህን ስሜት የምንዋጋው ዜጎች የኣንድነት ስሜታችንን በመንከባከብ ኢትዮጵያዊነትንን በመንከባከብ ነው። የዚህ ኦነግ ኣቋም ለብሄራዊ ስሜታችን መነሳሳት (revival) የራሱ ኣዎንታዊ ኣስተዋጻኦ ኣለው።

ደሞ ቸር ያሰማን
ገለታው ዘለቀ
http://us.mc338.mail.yahoo.com/mc/compose?to=geletawzeleke@gmail.com

No comments:

Post a Comment

Geletaw Zeleke's New Book *** ETHIOPIAN POLITICS የኢትዮጵያ ፖለቲካ

ይህ መጽሀፍ የማንነት ፖለቲካ እንዴትና ከየት እንደተነሳና ያለውን ችግሮች በዝርዝር ያስረዳል:: ዛሬ የኢትዮጵያ ሕዝብ ማህበረሰባዊ ግንኙነቶች ፈራርሰዋል። ደራሲው የሃገራችን መሰረታዊ ችግር የማህበረ ፖለቲካ ነው ይላል። ...