Friday, June 29, 2012

ስለ ሰላማዊ ዐመጽ7ነጥቦች!




1. የሰላማዊ ኣመጽ ብያኔ 
በቀላል ኣገላልጽ ሰላማዊ ኣመጽ ማለት  ኣክብሮት ጋር ኣንስማማም ማለት ነው። ይህምበመሆኑ ሰላማዊ ኣመጽ በኢትዮጵያ በምንም መለኪያ ከሽብርተኝነት ጋር ሊያያዝ ኣይችልም።ሰላማዊ ኣመጽ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገውንና የማይፈልገውን በግልጽ የሚያሳይበት ኣውድነው።
2. እውን ሰላማዊ ኣመጽ በኢትዮጵያ ሊሰራ ይችላልን?
የሰላማዊ ኣመጽን ታሪካዊ ኣመጣጥ ስናይ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ490 ኣካባቢ  ሮምእንደተጀመረ ኣዋቂዎች ይናገራሉ። ይህ የትግል ስልት ዘዴው እያደገ መጥቶ የቅርብ ጊዜየኣለማችንን ታሪክ እኳን ስናይ  1996 ጀምሮ እስከ 1999 የተለያዩ ሃገራት ህዝቦች በዚህየትግል ስልት ተጠቅመው ከኣምባገነን ስርኣቶች ለመላቀቅ ባደረጉት ትግል ከስልሳ ሰባቱ ሃምሳየሚሆኑት ኣመርቂ ውጤት እዳስመዘገቡ እናነባለን።

 ኣንዳንድ ወገኖች ሰላማዊ ኣመጽን ለማካሄድ ከመነሻው ትንሽም ቢሆን የፖለቲካ ክፍተት(political space) ሊኖር ይገባል፣ ትንሽም ቢሆን ህጋዊ ከለላ ያስፈልጋል ብለው ያምናሉ።ይህ መረዳት ከሰላማዊ ትግል ጋር ተደባልቆ የመጣ ሳይሆን ኣይቀርም።እውነት ነው ሰላማዊ ትግል ለማድረግ ትንሽ የፖለቲካ ምህዳር ያስፈልጋል። ሰላማዊ ኣመጽ ግን ከሰላማዊ ትግል የሚለይ ሲሆን በየትኛውም መንግስታት ይሰራል። በ ኦቶክራቶች፣ በኮሚኒስቶች፣በዴሞክራቶች፣ በነገስታት በሁሉም ሁኔታ ይሰራል።

  የኣጭር ጊዜ የኣለማችንን ታሪክ ስናይ በሰርቢያ  1998 (Otpor!) (ተቃውሞየተሰኘውየወጣቶች ሰላማዊ ኣመጽ ኣምባገነኑንና በቦስኒያ፣ ክሮሺያ እና ኮሶቮ በፈጸመው የጦር ወንጀልና በሰው ልጆች ላይ በፈጸመው (Crime against humanity) ወንጀል ተጠያቂ የሆነውንስሎቮዳን ሚሎሶቪክን ከስልጣን ለማውረድ የቻለ የትግል ስልት ነው። በሶቪየት ህብረት ጊዜየተነሱ የነጻነት ጥያቄዎች ውስጥ ይህ የትግል ስልት ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል። በፖላንድ፣በፊሊፒንስ፣ በሃንጋሪ፣ በቼኮዝሎቫኪያ፣ በቡልጋሪያ፣ በቺሊ ወዘተ. ተፈትኖ የወጣለት የትግልስልት ነው።
 ይህ የትግል ስልት በኢትዮጵያ የማይሰራበት ምንም ምክንያት የለም። ሰላምዊ ትግልበኢትዮጵያ ኣስቸጋሪ ወይም የማይቻል ብለው የሚያምኑ ወገኖች ሁሉ በሰላማዊ ኣመጽበኢትዮጵያ ለውጥ ኣይመጣም ማለታቸው ኣይደለም።

የኢትዮጵያ መንግስት ተፈጥሮና የፖለቲካው ኣጠቃላይ ከባቢም ቢሆን ይህን የትግል ስልት እንዳይነሳ የሚያደርገው ኣይደለም።


 3. ኢትዮጵያ ለሰላማዊ ኣመጽ የተዘጋጀች ኣገር ናት ወይ?
በኣጠቃላይ ህብረተሰብን ወደ ኣብዩትና ወደ ለውጥ  ከሚገፉት ጉዳዮች መካከል የሚከተሉትይጠቀሳሉ፣
    1. የድህነት መጨመር
    2. ኢፍትሃዊነት  ሰፊ  ኦፖርቹኒቲ እጦት፣ ስራ ኣጥነት፣ ኣድልዎ ወዘተ.
    3. ከፍተኛ የገቢ ኣለመመጣጠን (Large socio-economic disparities)
    4. የህዝቦች ሉኣላዊነት መደፈር
5. የኣንድነት መደፈርና 
6. የብሄራዊ ማንነት መነካት
7. የነጻነት እጦት
እነዚህ ከፍ ሲል የዘረዘርናቸውን ጉዳዮች ስናይ ኢትዮጵያ በነዚህ በሁሉም ጎኗ ቆስሏል።ኣልፎ ተርፎ የነዚህ ችግሮች ጡዘትም በዜጎች ልብ ውስጥ ተፈጥሮኣዊ የለውጥ ጥያቄንኣብስሏል። ይሁን እንጂ ለሁሉም ጊዜ ኣለው ታዲያ። በለስ ኣብቦ ያፈራና ሲበስል መቆረጥኣለበት። ጊዜው ሲያልፍ ጥቅም ኣይሰጥም። የህዝቦች የለውጥ ፍላጎት በከረረበት ሰኣት የሚነሳሰላማዊ ኣመጽ ውጤታማ ሲሆን እንዲሁ በየግለሰቡ ቤት እየተብሰለሰለ የሚያደራጀው ኣጥቶጊዜ ሲወስድ መጠውለግ፣ መደንዘዝ ያመጣል። ወይም ቁጣው ባልታቀደ መልኩ ይፈነዳናሊባክን ይችላል። ለዚህ ታዲያ ሃላፊነት የወሰዱ ሃይሎች ወቅቱንና የህዝቡን ብሶት ደረጃ እያዩ ማደራጀት ለሰላማዊ ኣመጽ ማነሳሳትና መምራት ይጠበቃል።

4. በሰላማዊ ኣመጽ የሚመጣ ለውጥ ለኢትዮጵያ ያለው ጠቀሜታ
1. ድሉ የራሱ የህዝቡ ስለሚሆን ውጤቱንም በንቃት ይከታተላል፣ይጠብቃል
      ህዝቡ በንቃት የተሳተፈበት ለውጥ ሁልጊዜም የሚኮራበት የሚደሰትበት ስለሚሆንበዚህ መንገድ የሚመጣ ለውጥ ጠቀሜታው የጎላ ነው
   2. ከሁሉም በላይ ለውጡን ከጥላቻ የጸዳ ስለሚያደርገው ከምንፈራው የ ክብ (vicious) በጥላቻ የተሞላ ትግል ወይም ጦርነት እንድንወጣ ኣዎንታዊ ሚና ይኖረዋል።
   3. ጸጋ ለመግለጥ
      የተለያየ ጸጋ ኣለን። ኣንዳንዱ ጥሩ ኣስተባባሪ ነው። ኣንዳንዱ ጥሩ መሪ ነው እነዚህጸጋዎች የሚገለጹበት ኣንዱ ኣውድ ይህ ህዝባዊ ኣመጽ ነው። ኣመጹ ሲነሳውስጣቸው ያለው ጸጋ እየገፋፋቸው ሃላፊነት እየወሰዱ የሚያስተባብሩ፣ የሚመሩሰዎች በዚያው ኣጋጣሚ ተስበው ቀጣዩን ለውጥ የሚመሩ ሊሆኑ ይችላሉ። ብዙታላላቅ መሪዎች በዚህ መንገድ ተፈጥረዋል። እውቁ የፍትህና የነጻነት ታጋይማርቲን ሉተር ኪንግ ኣመጽ የወለደው ነው።
4. ህብረትን ለማደስ
ሌላው ከህዝባዊ ኣመጹ ጋር ኣብሮ የሚገለጠው ነገር። ህብረትን ማደስ ኣንድነትን ማጠናከር ነው። የዜጎች ብሄራዊ ስሜት የሚበረታታበት፣ ፍቅርና መተሳሰብ የሚገለጥበት ኣውድ ነው።
5. ሰላማዊ ኣመጽ በኢትዮጵያ ምን መልክ ሊኖረው ይገባል? ማንስይምራው? ህዝብ ወይስ የፖለቲካ መሪዎች?
በኢትዮጵያ ውስጥ ህዝባዊ ኣመጽ በሁለት መንገድ የመነሳት እድል ኣለው ብለን እናስብ። ኣንደኛው የታቀደ በድርጅት የሚመራ ሲሆን ሁለተኛው ያልታቀደ በራሱ በህዝቡ የሚመራ። ከኢትዮጵያ ኣጠቃላይ የፖለቲካ ከባቢና ከተፈጠረው ስነ-ልቦናዊና መልካምድራዊ ክፍተትየተነሳ የታቀደው ቢሆን ሳይሻል ኣይቀርም። ያልታቀደ በህዝቡ የሚመራ ህዝባዊ ኣመጽበኢትዮጵያ ሁኔታ ሲታይ በዛ ያሉ እክሎች ያሉበት ይመስላል። ከነዚህም መሃል፣

 1. ኣመጹ በራሱ ከተቀሰቀሰ በሁዋላ የግድ የሆነ ቦታ ላይ ኣመራር መፈለጉ ኣይቀርምታዲያ በዚህ ጊዜ ተዘልለው ያሉም ይሁን ኣገር ቤት ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ምን ያህልህብረት ኣላቸው? ምን ያህል በኣመጹ ጊዜም ቢሆን ህብረት ፈጥሮ ኣመራር ለመስጠት ፈቃደኛናቸው? የሚለውን ጥያቄ ያመጣል። ድንገት የሚፈዳው የህዝብ ኣመጽ ኣመራር ሲፈልግ ከተለያዩ ኣካላት የተለያየ ኣመራር እየመጣ ግራ ማጋባት ያመጣስ ይሆን? ኣንዳንዶች ህዝቡ ኣብዩቱን ሲያቀጣጥለው ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ወደ ኣንድነት ይሳባሉ የሚል ኣሳብ ይኖራቸው ይሆናል። በርግጥ ይህ ኣይነቱ ተግባር በሰሜን ኣፍሪካው ኣብዮት ታይቷል። ነገር ግን የኢትዮጵያን የፖለቲካ ኣሰላለፍ ስናይ ከሰሜን ኣፍሪካው ስለሚለይ ይህ ኣሳብ ላያዋጣ ይችላል። ቀድሞ ህብረት መፍጠር በኢትዮጵያ ሁኔታ ኣዋጭ ነው።

 2. ከፍ ሲል እንዳልነው ባለፉት ኣመታት ከተፈጠረው የስነ ልቦና ክፍተት የተነሳ ኣንድቦታ ሳይታቀድ ቦግ ያለ ሰላማዊ ኣመጽ ሌላው የሃገሪቱ ክፍል ለመዛመት ምን ያህል እድልኣለው? ጎጃም የተነሳ ኣመጽ ናዝሬት ሊያስተጋባ ይገባዋል። ቡታጅራ የተነሳ ኣመጽ ጋምቤላኣሶሳ ሊያስተጋባ ሊቀበለው ይገባል። ይህ ካልሆነ በየጊዜው ኣንድ ኣካባቢ ቦግ የሚለው ኣመጽመንግስት እንዲቆጣጠረው ፋታ ይሰጠዋል። ችግሩንም በቀላሉ ለመቋቋም ያስችለዋል።
እንግዲህ ከነዚህ ጉዳዩች ኣንጻር ስናይ ነው በእቅድ የሚመራ ህዝባዊ ኣመጽ በኢትዮጵያማካሄድ ሳይሻል ኣይቀርም የሚያሰኘን ።


6. የታቀደ ህዝባዊ ኣመጽ ለመፍጠር ምን ያሻል?
የታቀደ ህዝባዊ ኣመጽ ለማነሳሳት የመጀመሪያው ተግባር የሃገሪቱን መልክና ተፈጥሮ የያዘህብረትና ኣመራር ነው መሰረቱ። ታዲያ ይህ ኣመራር በነሲብ በህብረት ስም በሩን ቡርቅቅኣርጎ መክፈት የለበትም። የኢትዮጵያን የፖለቲካ ትግል የጎዳው ኣፍጠው የመጡ የመንግስትደጋፊዎች ትግል ኣይደለም። በራሱ በመንግስት እጅ እየተደራጁ ትግሉን የሚያዳሙ (hijack)የሚያደርጉ ሃይሎች ናቸው። እውነተኛዎቹ ተቃዋሚዎች ደጋፊ እናጣለን በሚል ስጋት ሆዳቸውእያወቀ ዝም ማለት የለባቸውም።  እውነት ጋር ሲቆሙ የሚገርመው ህዝብ ኣሽትቶያውቀዋል።
በሃገራችን የገና ጨዋታ ጊዜ “ሚናህን ለይ” የሚባል ነገር ኣለ። ሚና ያለዩበት የገና ጨዋታእሩሯ የትም ኣትሄድም። እንዲሁ ሚናቸው ባለየላቸው ተጨዋቾች ተከባ ትቆያለች።

በቅንጅት ጊዜ በሚያዝያ ወር የታየው ታላቅ ትእይንት ተፈጥሮው ወደ ህዝባዊ ኣመጽ ያደላ ነበር። መንግስት ላፉ ፈቅጃለሁ ቢልም ትራንስፖርት በማሳጣት፣ በካድሬዎቹ ኣማካኝነት በማዋከብ ሰራተኛውን በማስፈራራት ሰልፉን መበተን ፈልጎ ነበር። ህዝቡ ግን ከኮልፌ ቀራንዩ ድረስ በእግሩ መጥቶ ሰልፉን ኣካሂዷል። በቅንጀት ህብረት ላይ ልቡ ስላረፈ፣ በመሪዎቹ ላይ እምነት ስላደረበት ኣውርድ የሚባለውን ለማውረድ ስቀል የሚባለውን ለመስቀል ዝግጁ ነበር። ይህ የሚያሳየው ህብረትና የሚያምነው ድርጀት ካገኘ ህዝቡ በእቅድ ለሚመራ ህዝባዊ ኣመጽ ወደሗላ የሚል ኣለመሆኑን ነው።

7. የሰላማዊ ኣመጹ ሲታቀድ ከግንዛቤ ሊገቡ የሚገባቸው ጉዳዮች

1. ህዝቡን በኣቅሙ የማታግል ስልት
  በኢትዮጵያ ሰላማዊ ኣመጽ ቀጣይነት ኖሮት  ለውጥ ለማምጣት እንዲችል የህዝቡንኣጠቃላይ ኣቅም ያገናዘበ መሆን ኣለበት። በመሆኑም ኣመጹ ሲታቀድ የህዝቡን ንቃተ ህሊና፣ኢኮኖሚ ሃይማኖትና ባህል ማገናዘብ መልካም ነው። ኣንድ ጊዜ የኣመጽ ኣይነቶችን ሁሉቢያሸክሙት የተሰጠውን የቤት ስራ እስከ መጨረሻ ላይወጣ ይችላል። ከሁሉም በላይ ቦግእልም እያለ ሩቅ ኣይሄድም። በየቀኑ ሰኳር የሚገዛን ህዝብ፣ በየቀኑ ጨው የሚገዛን ህዝብ፣በየቀኑ ዘይት እየገዛ የየቀን ኑሮውን ለመግፋት የሚታገልን ህዝብ ያየ የትግል ስልት ብዙ ብዙ ኣለ።

2. መቼት (setting)
የታቀደ ሰላማዊ ኣመጽ ሚስጥር ኣይደለም። ለሚሊዩን ህዝብ ተነግሮ ከመንግስት የሚደበቅነገር የለም። መቼና የት? ለሚለው ጥያቄ ግልጽ ምላሽ ሊኖረው ይገባል። ለኣብነት የምስራቅጀርመኖችን ታሪክ እናንሳ። በ1989  ምስራቅ ጀርመናዊያን ኣምባገነንነትን ለመቃወም ሲያቅዱ
“የሰኞ ኣብዮት” ብለው ተነሱ። በየሳምንቱ ምሽት ላይ በከተማይቱ መስቀል ኣደኣባይእየተገናኙ ለኣንድ ኣመት ያህል የዘለቀ ተቃውሞኣቸውን ኣድርገዋል። በዚያን ጊዜ ጀርመናዊያንሰኞን በናፍቆት እየጠበቁ ምን ላድርግ እያሉ እያሰቡ ይቃወሙ ነበር። እያደር ደጋፊያቸውእየበዛ ትግላቸው እያበበ ሄዶ በመጨረሻ የበርሊንን ግንብ ሳይቀር ለማፍረስ እና ለሁለቱጀርመኖች ውህደት በር ከፈተ። እቅዳቸው ኣቅማቸውን ጊዚያቸውን ያገናዘበ በመሆኑ ርቀትተጉዘው ኣሸነፉ።
በኢትዮጵያ የሚነሳ ህዝባዊ ኣመጽም እንዲህ መቼት ሊበጅለት ይገባል። መቼቱክርጀርመናውያን የተለየ ሊሆን ይችላል ግን ኣሁንም ቢሆን በኢትዮጵያ ሁኔታ መቼት መፍጠር ይቻላል።

3. ስያሜ
ህዝባዊ ሰላማዊ ኣመጽ መሪ ቃል ወይም ስያሜ ያሻዋል። በ1986 የኣለምን ቀንደና ሙሰኛየሆነውን ፈርዲናንድ ማርቆስን የፊኒፒንስ ህዝብ የጣለው የህዝብ ሃይል ኣብዮት “people power revolution” የሚል የትግል ስም ሰይመው ነው። ፊሊፒኖዎች መሪቃላቸውን ይዘውበየጎዳናው በጸሎትና በመዝመር ተቃውመው ማርቆስን ጥለዋል። በባልቲክ ግዛት በላቲቪያኤስቶኒያ የመዝሙር ኣብዮት “singing revolution” በሚል ስያሜ በዝማሬ ያለ ምንም ደምመፍሰስ የፈለጉትን ለውጥ ተቀዳጅተዋ።
በዚሁ በክፍለ ኣህጉራችን  2003 የላይቤሪያ ሴቶች በጸሎትና በመዝሙር ያደረጉትተከታታይ ተቃውሞ የላይቤሪያውያንን የርስ በርስ ጦርነት ለማስቆም ችሏል። በሊባኖስ “የዝግባኣብዩት”፣ በዩክሬን “ ብርቱካን ኣብዮት” በጆርጂያ “የጽጌረዳ ኣብዮት” ይጠቀሳሉ።በኢትዮጵያም ቀስቃሽና ነሻጭ የሆነ ስያሜ ቢሰጠው ለትግሉ ሃይል ይሆናል።

4. ትግሉ ሲጦዝ (Climax) ሊመጣ ችለውን ለውጥ ከግንዛቤ ኣስገብቶየታክቲክ ኣማራጮችን ቀድሞ ማስቀመጥ

  በኣንድ በተመረጠ መቼትና መሪ ቃል የሚጀመር ህዝባዊ ኣመጽ በኢትዮጵያ ውስጥመልኩን ሳይቀይር እስከመጨረሻ ላይጓዝ ይችላል።ኣመጹ እየበረታ ሲሄድ ደጋፊዎችሲበዙ በመንግስት በኩል ሪኣክሽን መፈጠሩ ኣይቀርም። በዚህ ጊዜም ትግሉኣቅጣጫውን ሊቀይር ስለሚችል ሊሆኑ የሚችሉትን ውጤቶች በመተመን ኣማራጭታክቲክ ቀድሞ ማሰብ የእቅዱ ኣካል ነው። በኣጠቃላይ እቅዱ ያሉትን ፍራቻዎች(threats)  መውጫቸውን ማስቀመጥ ኣለበት።

5.  መረጃ መቀባበያ ዘዴዎችን መፍጠር
መንግስት ህዝባዊ ኣመጽ ብቅ ሲል የመጀመሪያው ሩጫው የመረጃ መቀባበያ ዘዴዎችንመምታት ነው። ይህ እንደሚሆን ስለሚታወቅም መንግስት ሊቆጣጠራቸው የማይችሉ የመረጃመቀባበያ መንገዶችን መፍጠር ያስፈልጋል። በተለይ በገጠሩ ኣካባቢ ያለው ህዝብ ኣሰፋፈሩየተራራቀ ስለሆነ ለመረጃ የራሱን ባህል የተከተለ ዘዴ መፍጠር ተገቢ ነው። ለኣብነት ያህልበደቡቡ ያገራችን ክፍል ኣንድ ቀበሌ ህዝብ ሲያምጽ ወይም ችግር ሲደርስበት ከፍታ ቦታ ላይጭስ ያጨሳል ሌላው ቀበሌ ደሞ ተቀብሎ ለቀጣዩ ቀበሌ የሚታይ ቦታ ላይ ያጨሳል እንዲህእያለ ደቡብን ሊያደርስ ይችላል። እንዲህ ኣይነት ዘዴዎች በህዝቡ ባህል ውስጥ ስላሉ በቀላሉዓመጹን ማዳራስ ይቻላል። በከተማው ደሞ የተለየ መልክ ያለው ዘዴ መፍጠር ያሻል።
             እግዚኣብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!
             geletawzeleke@gmail.com
                 ገለታው ዘለቀ

http://www.ethiopianreview.com/research/5539
http://en.wikipedia.org/wiki/Nonviolent_resistance

No comments:

Post a Comment

Geletaw Zeleke's New Book *** ETHIOPIAN POLITICS የኢትዮጵያ ፖለቲካ

ይህ መጽሀፍ የማንነት ፖለቲካ እንዴትና ከየት እንደተነሳና ያለውን ችግሮች በዝርዝር ያስረዳል:: ዛሬ የኢትዮጵያ ሕዝብ ማህበረሰባዊ ግንኙነቶች ፈራርሰዋል። ደራሲው የሃገራችን መሰረታዊ ችግር የማህበረ ፖለቲካ ነው ይላል። ...